Awash Insurance company S.C

የአዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ትርፍ(2015/16)

Posted by admin  •  November 08, 2016

አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከብር 104.6 ሚሊዮን በላይ አተረፈ::

  • ከግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች የገበያ መሪነቱን ለአራተኛ ተከታታይ ዓመታት አረጋገጠ::

አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. በተጠናቀቀው በጀት ዓመት (ጁን 30፣ 2016 ዓ.ም.) ከታክስ በፊት ያልተጣራ ብር 104.6 ሚሊዮን አተረፈ፡፡ የኩባንያው የዓመቱ የተጣራ ትርፍ 91.15 ሚሊዮን ሆኖ በዓመቱ የላቀ ውጤት ተመዝግቧል፡፡ ከትርፍ ግብር በኋላ ደግሞ ካለፈው ዓመት የተጣራ ትርፍ ጋር ሲነጻጸርም የ41 በመቶ እድገት አስመዝግቧል፡፡

ኩባንያው በጠቅላላ መድን ሥራ /General Insurance/ ከ479 ሚሊዮን ብር በላይ አረቦን ገቢ በመሰብሰብ የ18.5 በመቶ እድገት ሲያስመዘግብ በሕይወት መድን /Life Assurance/ ደግሞ ብር 45 ሚሊዮን አረቦን በመሠብሠብ የ13 በመቶ ዕድገት በማሳየት አበረታች ውጤት አስመዝግቧል፡፡

በበጀት ዓመቱ የተገኘው ውጤት ኩባንያው ከግል የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በሁለቱም የስራ ዘርፎች ማለትም በጠቅላላ መድን ሥራ ዘርፍና በሕይወት ኢንሹራንስ በአጠቃላይ የአረቦን ገቢ ግንባር ቀደም በመሆን የገበያ ድርሻውን በመሪነት ማስቀጠል አስችሎታል፡፡ ይህ የገበያ መሪነት ለበርካታ ዓመታት በተከታታይ የተመዘገበ መሆኑ የኩባንያውን ጥንካሬ ያረጋግጣል፡፡

የኩባንያው ዓመታዊ የሽያጭ ገቢ ዕድገት ከላይ የተቀመጠውን ሲመስል፤ በሥራ ዓመቱ በጠቅላላ መድን ሥራ ዘርፍና በሕይወት ኢንሹራንስ ዘርፍ ብር 245 ሚሊዮን የካሳ ክፍያ /Net Claims Incurred/ አጋጥሞታል፡፡

አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ከኡራኤል ወደ ቦሌ መድኃኒዓለም በሚወስደው መንገድ ላይ ሁለት ቤዝመንቶችንና ግራውንድ ፍሎሩን ጨምሮ ባለ 10 ፎቅ ጅምር ህንጻ በቀደመው በጀት ዓመት ገዝቶና በቅርቡ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ደግሞ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ግንባታውን አጠናቆ አገልግሎት ላይ ለማዋል በቅቷል፡፡

ኩባንያው ሁለት አዳዲስ ቅርንጫፎችን በአዲስ አበባ ከተማ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አዲሱ ገበያ አካባቢ እና በየካ ክፍለ ከተማ መገናኛ አካባቢ በመክፈት ለኢንሹራንስ ተጠቃሚው ህብረተሰብ የበለጠ ተደራሽ ለመሆን ችሏል፡፡ እነዚህን አዳዲስ ቅርንጫፎችና ሌሎች ሁለት አገናኝ ቢሮዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ የኩባንያው ቅርንጫፎች ብዛት 41 በመድረሱ በዚህ ረገድም ከግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች አዋሽ ኢንሹራንስ ግንባር ቀደም ነው፡፡

አዋሽ ኢንሹራንስ 3ኛውን የአምስት ዓመታት ስትራቴጂክ እቅድ በዚሁ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ቀርጾና አጽድቆ ስራ ላይ አውሏል፡፡

በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ውጤቶች አጠቃቀም ረገድ አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ የሀብት አስተዳደሩን ዘርፍ አዲስ ሶፍትዌር በማበልጸግ በመረጃ መረብ የተሳሰረ ስራ ለመስራት መቀመጫውን በህንድ ካደረገ ኢንፎዥን ከተባለ የሶፍትዌር ኩባንያ ጋር የ3.3 ሚሊዮን ብር አዲስ ውል ተፈራርሟል፡፡ ከዚህ የህንድ ኩባንያ ጋር ቀደም ሲል በስኬት የተጠናቀቀ በኢንሹራንስ ኢንዱስትሪው ታሪክ ፈር ቀዳጅ የሆነ አዲስ ሶፍትዌር በማበልፀግ ስራ ላይ በማዋል የኩባያውን ዋና መ/ቤት የስራ ክፍሎች እና ቅርንጫፎች በመረጃ መረብ በማገናኘት እጅግ የዘመነ ኢንፎርሜሽን ሲስተም ስራ ላይ ለማዋል የቻለ ኩባንያ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ፈሰስ በማድረግ በ33.2 ሚሊዮን ብር ከአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ፤ ከአገራዊ የጠለፋ ዋስትና ድርጅት ከኢትዮ-ሪ ደግሞ በ25 ሚሊዮን ብር አክሲዮኖችን ገዝቷል፡፡ በነዚህ ሁሉ ጥረቶች ለኩባንያው ባለሀብቶች የማይነጥፍ የገቢና የትርፍ ምንጭ ለመፍጠርና ለማስፋፋት የተለያየ የኢንቨስትመንት ጥረቶች ተደርገዋል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አዋሽ ኢንሹራንስ 70 የሽያጭ ወኪሎችን በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት አሰልጥኖ ያስመረቀ ሲሆን ሁሉም ተመራቂዎች የሽያጭ ውክልና ፈቃድ አውጥተው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የአዋሽ ኢንሹራንስ የሽያጭ ወኪሎች ቁጥር ከ370 በላይ ደርሷል፡፡    

የኩባንያው የቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ብዛት አንድ የሕይወት ቅርንጫፍን ጨምሮ 41 ሲሆን የሰራተኞች ቁጥርም 444 ደርሷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የኩባንያችን የተከፈለ ካፒታል ብር 200 ሚሊዮን በላይ ሆኗል፡፡

-------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------- 

አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ..(..) መስከረም 20 ቀን 1987 .፣ም፣ ከመነግስት የንገድ ፈቃድ እገኘ፡ ተሀሳስ 23 ቀን 1987 .. በይፋ ስራዉን ጀመረ። አ.ኢ.ኩ. በአገራችን የኢንሹራንስ ኢንደስትሪ ታሪክ በጠንካራና ልዩ ማሕበረሰባዊ ስብጥር ላይ የተገነባ የመጀመሪያው መሰረተ ሰፊ የግል ኢንሹራንስ ኩባንያ ነው፡፡ ባለአክሲዮኖቹ በምሥረታ ወቅት 456 የነበሩ ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት ብዛታቸው 1209 ደርሷል፡፡ Financial Results
​Awash Insurance Company S.C. latest financial results. Read More

የአዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ትርፍ(2015/16)
​አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከብር 104.6 ሚሊዮን በላይ አተረፈ:: Read More

The CEO Is Awarded Doctor of Business Administration(DBA) Degree.
Tsegaye Kemsi Aredo, the CEO of Awash Insurance Company S.C. is awarded degree of Doctor of Business Administration(DBA) Specializing in Insurance Management Honoris Causa  by the prestigious Common Wealth University. Read More

አዋሽ ኢንሹራንስ በግማሽ ዓመት አፈጻጸም ::
አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ የግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ከጥር 27 እስከ ጥር 29 ቀን 2008 ዓ.ም በሶደሬ ሪዞርት ሆቴል በካሄደበት ወቅት ኩባንያው በግማሽ ዓመቱ ከጠቅላላ ኢንሹራንስ ዘርፍ ብቻ ብር 246 ሚሊዮን አረቦን መሰብሰቡን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀጋዬ ከምሲ ገለጹ፡፡

Read More

AIC Earns a Premium of 267 Million in the Mid-Year.
AIC staff became shareholders.The mid-year performance review Meeting of Awash Insurance Company for the year 2015 - 16 was held at Sodere Resort Hotel, from February 5 - 7, 2016.

Read More

CalendarSeptember 2017

M T W T F S S
        1 2 3
4 5 6 7 8 9 10
11 12 13 14 15 16 17
18 19 20 21 22 23 24
25 26 27 28 29 30  
             

Contact Information

Awash Insurance Company S.C.
Awash Towers,
Ras Abebe Aregay Street,

Kirkos subcity,Woreda 7
Tel.  +251-011 5 57 00 01
Fax: +251-011 5 57 02 08

E-mail: aic@ethionet.et/aic@awashinsurance.com
P.O.Box 12637
Addis Ababa, ETHIOPIA

Follow Us