አዋሽ ኢንሹራንስ “እምነትዎን ስለጣሉብን እናመሰግናለን” በሚል መሪ ቃል የደንበኞች ሳምንት በማክበር ላይ ይገኛል። በዓሉ በሁሉም የኩባንያችን ቅርንጫፎች እና አገናኝ ቢሮዋች ለአንድ ሳምንት በተለያዩ ደማቅ ፕሮግራሞች ይከበራል። ከሰላሳ አመታት በላይ በነበረን የመድን ሽፋን አገልግሎታችን ላይ ከፍተኛ እምነት ጥለዉብን ከኛ ጋር ለተጓዙ፣ የእድገት እና የስኬታችን ጠንካራ መሰረት የሆኑ ደንበኞቻችንን ከልብ እያመሰገንን፣ በዓሉን ምክኒያት በማድረግ ለደንበኞቻችን የተለያዩ ስጦታዎችን አዘጋጅተናል።
- በተለያዩ የኢንሹራንስ አገልግሎቶች ላይ እስከ 25% የሚደርስ እና ለአንድ ወር የሚቆይ ቅናሽ ተደርጓል። ለምሳሌ በ Mortgage Redemption Insurance (MRI)፣ Individual Life Insurance፣ በትምህርት ኢንሹራንስ፣ በሰራተኞች ኢንሹራንስ (Workers’ Compensation Insurance) እና በእሳት አደጋና መብረቅ ኢንሹራንስ ላይ 25% ቅናሽ ተደርጓል።
- ወደ አዋሽ ኢንሹራንስ ዋና መስሪያ ቤት፣ ቅርንጫፎች እና አገናኝ ቢሮዎች በመምጣት ለተሽከርካሪያቸው ሙሉ የመድን ሽፋን ለሚገዙ ደንበኞች አስገዳጅ የሶስተኛ ወገን ሽፋን በሕግ የተቀመጠውን አረቦን ለከፈሉ ደንበኞች ተጨማሪ ዋስትና ይሰጣል፣ በሶስተኛ ወገን ለሚደርስ ጉዳት ብር 200,000 የነበረዉ የንብረት ካሳ ሽፋን (Property Coverage) ወደ ብር 300,000 ያድጋል፣ ብር 250,000 የነበረ የሶስተኛ ወገን የሞት እና የአካል ጉዳት ካሳ ሽፋን ወደ ብር 300,000 ያለ ተጨማሪ አረቦን ክፍያ ያድጋል። ከዚህ በላይ በተገለጸዉ ጊዜ ወስጥ ወደ ኩባንያችን ወና መስሪያ ቤት፣ ቅርንጫፎች እና አገናኝ ቢሮዋች በመምጣት የመድን ዋስትና አገልግሎት የሚገዙና የሚያድሱ ነባር ደንበኞችም ሆነ አዳድስ ደንበኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
- በኩባንያችን የመሃበራዊ ትስስር ገጾች ማለትም በፌስቡክ፣ በቴሌግራም እና በሊንክድ ኢን በሚደረጉ የመድን ዋስትና አገልግሎት ግንዛቤ ማስጨበጫ ጫወታዎች ላይ በመሳተፍ ያሸነፉ ደንበኞቻችን የተለያዩ መጠን ያላቸዉ የሞባይል ካርድ ይበረከታል።
የኩባንያችን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጅባት አለምነህ ባደረጉት ንግግር ሁሉንም የበዓሉ ታዳሚዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት አዋሽ እንሹራንስ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ደንበኞቹን የኩባንያዉ “የስኬቶቹ ጠንካራ መሰረት” መሆናቸውን ተረድቶ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና እየተለዋወጠ የሚሄደዉን የደንበኞቹን ፍላጐት ለማርካት መሰረተ ሰፊ የሆኑ የተለያዩ ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጿል፡፡ ይህም የኩባንያው የመድን ዋስትና ሽፋን አገልግሎት ተመራጭ፣ አስተማማኝ እና ኩባንያው በሀገራችን ካሉት ሁሉም የግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ቀዳሚው እንዲሆን ያስቻሉ ሲሆን ከ90 ሺ በላይ የሆኑ ደንበኞችን እንድናፈራ አስችለዉናል ብሏል። አቶ ጅባት አክለዉም ደንበኞቻችን በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀላቸዉ ስጦታዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስታወስ፣ ወደ ፊት ለሚጠብቀን ሌላኛው የአብሮነትና ስኬታማ ጉዙ በመጋበዝ ለነበራቸው ቆይታ ከልብ አመስግኗል።
የኩባንያችን ዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ ገመዳ በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር አድርጎ የክብረ በዓሉን መጀመር በታላቅ ደስታ አብስረዋል። አቶ ታደሰ ባደረጉት ንግግር ኩባንያው ከምስረታው ጀምሮ ለደንበኞች አገልግሎት በሰጠዉ ትኩረት ከደንበኞች ከፍተኛ እምነት ማግኘት መቻሉን እና በቪዥን 2030 ስትራቴጂ የላቀ የደንበኞች አገልግሎትን እውን ለማድረግ ዝርዝር ዕቅዶች አውጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጽዋል። በመሆኑም በደንበኞች ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ የመድን ዓይነቶችን በመቅረፅ ለደንበኞች የማቅረብና የደንበኞችን እርካታ ለማረጋገጥ የሚረዱ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት (Service Delivery Standards) በማዘጋጀት በሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረጉንም አስታውሰዋል። “ደንበኞች የህልውናችን መሰረት ናቸው” ያሉት አቶ ታደሰ፣ ኩባንያው በየጊዜው የደንበኞች ጉብኝት( Customers Visit) በማድረግ ከደንበኞች የሚገኙ ግብረመልሶች እየተወሰዱ የኩባንያው አገልግሎት እንዲሻሻል የሚደረግበት አሰራር መኖሩን ገልጸዋል፡፡
ለመላዉ የኩባንያችን ደንበኞች መልካም የደንበኞች ሳምንት እንመኛለን!