Blog Detail

አዋሽ ኢንሹራንስ 2.4 ቢሊየን ብር አረቦን ሰበሰበ!

አዋሽ ኢንሹራንስ 2.4 ቢሊየን ብር አረቦን ሰበሰበ!

አዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 2.4 ቢሊዮን ብር አረቦን በመሰብሰብ ከግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ሁሉ ዛሬም እንደ ትላንቱ አንደኝነቱን አስመስክሯል፡፡ ኩባንያችን በበጀት ዓመቱ በጠቅላላ መድን (General Insurance) ሥራ 2 ቢሊዮን ብር በላይ አረቦን ገቢ የሰበሰበ ሲሆን በዚህ ዘርፍም የ 66 በመቶ የሽያጭ ገቢ እድገት አስመዝግቧል፡፡ በሕይወት መድን (Life Assurance) ስራ ዘርፍ ከብር 275 ሚሊዮን በላይ አረቦን ገቢ በማግኘት የ47 በመቶ ዕድገት ሲያስመዘግብ በተካፉል ዘርፍ ደግሞ 40 ሚሊየን አረቦን ገቢ በማግኘት የ357 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡

በግል ኢንሹራንስ ዘርፍ ፈር ቀዳጅ ከሆኑት ኩባንያዎች አንዱ የሆነው አዋሽ ኢንሹራንስ ከሁለት አመት በፊት አለም አቀፍ አማካሪ በሆነው ዲሎይት የአስር አመት መሪ እቅዱን አስጠንቶ ተግባር ላይ ማዋል የጀመረ ሲሆን፣ ይህም ኩባንያው በተጠናቀቀው ዓመት ላስመዘገበው ውጤት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው ተገልጻል፡፡
በቅርቡ የድርጅት መለያ ለውጥ (Rebrand) ያደረገው አዋሸ ኢንሹራንስ በአዲስ ገፅታ እና በታደሰ ቃል ኪዳን “ከእርስዎ ጋር…” የሚል መሪ ቃል ይዞ ለደንበኞቹ ከመቼውም ጊዜ በላቀ መልኩ አጋርነቱን በማጠናከር የላቀ እርካታን ለማረጋገጥ ከደንበኞቹ ጋር ወደፊት በመገስገስ ላይ ይገኛል፡፡

ከግል ኢንሹራንስ ገበያ መሪነቱ ጎን ለጎን በኢንቨስትመንት ዘርፉ ተሳትፎውን ለማጠናከር አዋሽ ኢንሹራንስ የኢንቨስትመንት አድማሱን በማጎልበት እና ተደራሽነቱን ከማስፋት አንጻር የፋይናንሻል ኩባንያዎች ማዕከል በሆነው በመሀል ሜክሲኮ አዲስ የዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ (B+G+35) ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጿል፡፡
ድርጅቱ ልክ እንዳለፉት አመታት ሁሉ በኢንዱስትሪው ውስጥ በግል ኢንሹራንስ ዘርፍ ያለውን መሪነት አስጠብቆ እንዲቀጥል ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደረጉት በድርጅቱ ላይ እምነታቸውን በመጣል ሲገለገሉ የቆዩት ደምበኞቹን ከልብ በማመስገን ለቀጣዩ አመታትም በአዲስ ገፅታና በታደሰ ቃልኪዳን የደምበኞችን ፍላጎት ሁሉ ለማሟላት ከፍተኛ ጥረት የሚያደርግ መሆኑን ገልጿል፡፡ በተጨማሪም በዓመቱ ለተገኘው አመርቂ ውጤት የኩባንያው የሥራ መሪዎችና መላው ሠራተኞች ላደረጉት አስተዋፅዖ ከፍተኛ ምስጋና ኩባንያው አቅርቧል፡፡