30th ANNUAL ORDINARY AND 12th EXTRAORDINARY GENERAL MEETINGS OF SHAREHOLDERS
Notice is hereby given to the Shareholders to attend the 30th Annual Ordinary and 12th Extraordinary General Meetings of Awash Insurance S.C. which will be held in accordance with Article 393(1) and Article 400(1) of Commercial Code of Ethiopia, Proclamation Number 1243/2021 as well as Article 8(a) of the Memorandum of Association of the Company. Awash Insurance S.C. has a subscribed capital of Birr 3,850,185,500 and paid-up capital of Birr 1,921,492,300 as at June 30, 2024; Business Registration Certificate Number of the Company is አአ/ገግ-3-1532/87 from the Trade Bureau, Insurance Business License Number 003/94 issued by the National Bank of Ethiopia, and the Company’s Headquarters is at Awash Towers, Addis Ababa, Kirkos Subcity, Woreda 7. The General meetings will be held on Saturday, October 26, 2024 at Addis Ababa Hilton Hotel starting from 8:00 a.m. to transact the following business:
AGENDA FOR 30th ANNUAL ORDINARY GENERAL MEETING
- Notification of Share Transfers, Share Sales and New Shareholders who acquired shares in 2023/24;
- Consideration and approval of the 2023/24 Annual Report of Board of Directors;
- Consideration and approval of the 2023/24 Annual Report of Auditors;
- Deliberation on and approval of the proposed appropriation of 2023/24 profits;
- Approval of Annual Compensation of Board of Directors for 2023/24;
- Approval of Board of Directors’ monthly allowance for 2024/25;
- Approval of the Auditors’ Annual Fee for 2024/25; and
- Election of the members of Board Nomination and Election Committee.
AGENDA FOR 12th EXTRAORDINARY GENERAL MEETING
- Amendment of the Memorandum of Association of Awash Insurance S.C.
N.B.
Shareholders who are not able to attend the meetings in person may sign and return the proxy form and give one copy to the designated agent and the second copy along with the copy of renewed identification card of a shareholder to be submitted to the Company’s CEO office, on the 2nd floor of Awash Towers, three days before the meeting date.
By Order of the Board of Directors
የባለአክሲዮኖች 30ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔና 12ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ
የአዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች በኢትዮጵያ ንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 393(1) እና አንቀጽ 400(1) እንዲሁም በኩባንያው መመስረቻ ፅሁፍ አንቀጽ 8(ሀ) መሠረት በሚደረገው 30ኛ ዓመታዊ መደበኛና 12ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔዎች ላይ እንዲገኙ መስታወቂያ ተሰጥቷል።
ኩባንያው የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ቁጥር አአ/ገግ-3-1532/87 ከንግድ ቢሮ እንዲሁም የመድን ሥራ ፍቃድ ቁጥር 003/94 ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሰጠው ሲሆን እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2024 ላይ የኩባንያው የተፈረመ ካፒታል ብር 3,850,185,500፣ የተከፈለ ካፒታል ብር 1,921,492,300 ደርሷል።
የኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አዋሽ ታወርስ ላይ ይገኛል። ጠቅላላ ጉባዔዎቹ ቅዳሜ ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄዱ ሲሆን የሚከተሉት አጀንዳዎች ላይ ይወያያል፣
የ30ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳ
- እ.ኤ.አ. በ2023/24 የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮች፣ የአዲስ አክሲዮኖች ሽያጭና አዲስ ባለአክሲዮኖችን ማሳወቅ፣
- እ.ኤ.አ. የ2023/24 የዲሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ፣
- እ.ኤ.አ. የ2023/24 የኦዲተሮች ዓመታዊ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ፣
- እ.ኤ.አ. የ2023/24 የትርፍ ክፍፍል ላይ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ማፅደቅ፣
- እ.ኤ.አ. የ2023/24 የዲሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ክፍያ መወሰን፣
- እ.ኤ.አ. የ2024/25 የዲሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበል መወሰን፣
- እ.ኤ.አ. የ2024/25 የኦዲተሮችን ዓመታዊ ክፍያ መወሰን፣
- የዲሬክተሮች ቦርድ የምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ማካሄድ።
የ12ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳ
-የአዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ. መመስረቻ ጽሁፍ ማሻሻል።
ማሳሳቢያ
በጉባዔዎቹ ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች የውክልና ፎርሙን ፈርመው በመመለስ አንድ ኮፒ ለተመደበው ወኪል እንዲሁም 2ኛውን ኮፒ ከታደሰው የባለአክሲዮኑ መታወቂያ ካርድ ጋር በማያያዝ ለጉባዔዎቹ 3 ቀናት ሲቀረው አዋሽ ታወርስ 2ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ማስገባት ይችላሉ።
በዲሬክተሮች ቦርድ ትዕዛዝ